Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 14:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የሰረገሎቹንም ጎማ አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አስገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “ጌታ ግብፃውያንን ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 መንዳት እንዳይችሉም የሠረገላዎቹን መሽከርከሪያዎች አቈላለፈባቸው፤ ግብጻውያኑም፣ “ከእስራኤላውያን እንሽሽ! እግዚአብሔር ግብጽን እየተዋጋላቸው ነው” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እግዚአብሔር የሠረገላዎቻቸውን መንኰራኲሮች ከመሬት ጋር ስላጣበቀባቸው ሠረገሎቻቸውን ነድተው ማንቀሳቀስ አልቻሉም፤ ግብጻውያንም፥ “እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ረድቶ እኛን እየተዋጋን ነው፤ ስለዚህ ከፊታቸው እንሽሽ!” ተባባሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም መን​ኰ​ራ​ኵር አሰረ፤ ወደ ጭን​ቅም አገ​ባ​ቸው፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ ይዋ​ጋ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እን​ሽሽ” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የሰረገሎቹንም መንኮራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ፤” አሉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 14:25
26 交叉引用  

ጌታ የእስራኤልን ጠላቶች እንደ ወጋ በሰሙ ጊዜ በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ የጌታር ፍርሃት አደረባቸው።


የቀንደ መለከቱን ድምፅ በምትሰሙበት ስፍራ በዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል።”


እንዲህም ሆነ፦ ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ ዓይናቸውም እያየ ብዙ ውድቀት ሆነ፥ ይህ ሥራ በአምላካችን እንደ ተከናወነ አወቁ።


በፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ተሻገሩ፤ አሳዳጆቻቸውን ግን በኃይለኛ ውኃ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ጣልካቸው።


የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥ የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥ ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”


ከብረት መሣሪያም ቢሸሽ፥ የናስ ቀስት ይወጋዋል።


ነፋሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፥ እርሱ ግን ከእጁ ፈጥኖ ለመሸሽ ይታገላል።


የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ የሚከሱኝን ክሰሳቸው፥ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።


የጌታን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።


ጌታ ትእዛዙን ሰጠ፥ የሚያበሥሩት ብዙ ሠራዊት ናቸው።


ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥ እንቅልፋቸውንም አንቀላፉ፥ የጦር ሰዎች በሙሉ በእጃቸው ምንም ማድረግ አልቻሉም።


ጌታ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ።”


ግብፃውያንም በፈርዖንና በሰረገሎቹ በፈረሰኞቹም ላይ ክብር ባገኘሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።”


እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፥ እርሱም ያሳድዳቸዋል፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ ላይ ክብር አገኛለሁ፤ ግብፃውያንም እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።


ጌታ ተዋጊ ነው፥ ስሙም ጌታ ነው፤


ጌታም እንዲህ ይለኛልና፦ አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሣ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንደዚሁም የሠራዊት ጌታ በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ለመዋጋት ይወርዳል።


በአንቺ ፈረሱንና ፈረሰኛውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሠረገላውንና በላዩ የሚቀመጠውን እሰባብራለሁ፤


በረባት ቅጥር ላይ እሳትን አነዳለሁ፤ በጦርነትም ቀን በጩኸት፥ በዐውሎ ነፋስም ቀን በሁከት የእርሷን የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤


ከአንበሳ ፊት ሲሸሽ ድብ እንዳገኘው ሰው፥ ወይም ወደ ቤት ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ነው።


ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፦ መድረኮቹ እስኪናወጡ ድረስ ጉልላቶቹን ምታ፥ በሰዎቹም ራስ ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፤ እኔም ከእነርሱ የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ፤ የሚሸሽ አያመልጥም፥ የሚያመልጥም አይድንም።


በዓይናችሁ ፊት በግብጽ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ በፊታችሁ የሚሄደው ጌታ አምላካችሁ ስለ እናንተ ይዋጋል፤


ጌታ አምላካችሁ እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋልና አትፍሯቸው።”


ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም።


ጌታ ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና ጌታ የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።


ጌታም ሲሣራንና ሠረገሎቹን ሁሉ በባራቅ ፊት በሰይፍ ስለት እጅግ ተሸንፈው ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ አደረገ፤ ሲሣራም ከሠረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።


跟着我们:

广告


广告