Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን ከኋላቸው እየመጡ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ ጌታም ጮኹ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ፈርዖን በቀረበ ጊዜ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ እነሆ፣ ግብጻውያን ይከታተሏቸው ነበር፤ እነርሱም በታላቅ ፍርሀት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እስራኤላውያን ንጉሡና ሠራዊቱ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል መምጣታቸውን አይተው እጅግ ፈሩ፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዐይናቸውን አነሡ፤ እነሆም ግብፃውያን በኋላቸው ገሥግሠው ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ።

参见章节 复制




ዘፀአት 14:10
23 交叉引用  

የሰረገሎችም አለቆች ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ፦ “የእስራኤል ንጉሥ ነው” አሉ፥ ሊወጉትም ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥ ግን ጮኸ፥ ጌታም ረዳው፥ አምላኩም ከእርሱ መለሳቸው።


“በግብጽ የአባቶቻችንን መከራ አየህ፥ በቀይ ባሕርም ጩኸታቸውን ሰማህ፤


እርሱ ግን ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ ጭንቃቸውን ተመለከተ፥


በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።


በተጨነቁ ጊዜም ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከጭንቀታቸው አዳናቸው።


በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።


በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው፥


መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የጌታ ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ተነሥቶአል።


እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።


ጫንቃውን ከሸክም፥ እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ።


እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ቅርብ ቢሆን በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብጽም እንዳይመለስ” ብሏልና።


እርሱም ወደ ጌታ ጮኸ፤ ጌታም ዛፍ አሳየው፥ በውኃውም ላይ ጣለው፥ ውኃውም ጣፋጭ ሆነ። ጌታም በዚያ ሥርዓትንና ፍርድን አደረገላቸው፥ በዚያም ፈተናቸው፤


አቤቱ ጌታ፥ በመከራ ጊዜ ፈለጉህ፥ በገሠጽሐቸውም ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።


ለዳዊት ቤት፤ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፤ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ።


አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕመም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታቃስቻለሽ!”


“ጌታ አምላክህን በምድረ በዳ እንዴት እንዳስቆጣኸው፥ ከግብጽ ምድር ከወጣህበት ቀን ጀምሮ እዚህ ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በጌታ ላይ እንዳመፃችሁ አስታውስ፥ አትርሳም።


አባቶቻችሁንም ከግብጽ አወጣኋቸው፥ ወደ ባሕሩም ደረሳችሁ፤ ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አባረሩአቸው።


ወደ ጌታም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብጽ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።


በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሃት ቅጣት አለው፥ የሚፈራ ሰው በፍቅር ፍጹም አልሆነም።


跟着我们:

广告


广告