Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሰባት ቀንም ሙሉ ያልቦካ ቂጣ ትበላለህ፥ በአንተም ዘንድ እርሾ ያለበት አይታይ፥ በድንበርህም ሁሉ እርሾ አይታይ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በእነዚህም ሦስት ቀናት ቂጣ ትበላላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ እርሾ ያለበት ነገር ፈጽሞ አይገኝ፤ በምድራችሁም አዋሳኝ በየትኛውም ቦታ እርሾ ፈጽሞ አይኑር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እስከ ሰባት ቀን ድረስ ያልቦካ እንጀራ ትበላላችሁ፤ እርሾም ሆነ የቦካ እንጀራ ከቶ በምድራችሁ አይገኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ እርሾ ያለ​በት እን​ጀራ አይ​ታይ፤ በአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ እርሾ አይ​ኑር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፤ በአንተም ዘንድ እርሾ ያለበት እንጀራ አይታይ፤ በድንበርህም ሁሉ እርሾ አይታይ።

参见章节 复制




ዘፀአት 13:7
6 交叉引用  

ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።


ሰባት ቀን በቤታችሁ እርሾ አይገኝ፤ እርሾ ያለበትንም እንጀራ የሚበላ ነፍስ፥ ከመጻተኛው ጀምሮ እስከ አገሩ ተወላጅ ድረስ፥ ከእስራኤል ማኅበር ተለይቶ ይወገድ።


ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” አላቸው።


ስለዚህ ተንኰልና ክፋት በሞላበት በአሮጌ እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት የቅንነትና የእውነት ቂጣ በዓላችንን እናክብር።


በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቆይ አታድርግ።


ከፋሲካውም በኋላ በማግስቱ የምድሪቱን ፍሬ እርሾ ያልገባበትን የቂጣ እንጎቻና ቆሎ በዚያው ቀን በሉ።


跟着我们:

广告


广告