Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 12:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “ይህ የፋሲካ ሥርዓት ነው፤ ማንም እንግዳ ሰው ከእርሱ አይብላ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ በዓል አከባበር ሥርዐት እንዲህ ነው፤ ባዕድ የሆነ ሰው ከፋሲካው ምግብ አይብላ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ በዓል አከባበር ሥርዓት ይህ ነው፤ ማንኛውም የባዕድ አገር ሰው የፋሲካን ራት አይብላ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን አለ “ይህ የፋሲካ ሕግ ነው፤ ከእርሱ እንግዳ ሰው አይብላ።

参见章节 复制




ዘፀአት 12:43
9 交叉引用  

እንደ ትእዛዙም ሳይሆን ከኤፍሬምና ከምናሴ ከይሳኮርና ከዛብሎንም ወገን እጅግ ብዙ ሰዎች ሳይነጹ ፋሲካውን በሉ። ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እንዲህ ብሎ ጸለየ፦ “ቸሩ ጌታ ሆይ! ሁሉንም ሰው ይቅር በል፤


እንግዲህ ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ብሉት፤ ለጌታ ፋሲካ ነው።


እንግዳ ሰውም በመካከላችሁ ቢቀመጥ ለጌታም ፋሲካን ሊያደርግ ቢፈልግ፥ እርሱና የእርሱ ወንዶች ሁሉ ይገረዙ ከዚያም ይቅረብ ያድርግም፤ እንደ አገሩ ተወላጅም ይሆናል፤ ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ።


ምግቤን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ ቤቴን እንዲያረክሱ በመቅደሴ ውስጥ እንዲሆኑ ያልተገረዘ ልብ፥ ያልተገረዘ ሥጋ ያላቸውን ባዕዳንን አግብታችኋል፥ በርኩሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል።


“ማናቸውም ምእመን ከተቀደሰው አይብላ የካህኑም እንግዳ የሆነ እና ተቀጥሮ የሚያገለግል ከተቀደሰው አይብላ።


የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ማናቸውም ምእመን ግን ከእርሱ አይብላ።


በመካከላችሁም መጻተኛ ቢኖር፥ ለጌታም የፋሲካን በዓል ቢያከብር፥ እንደ ፋሲካ ሥርዓትና እንደ ደንቡ እንዲሁ ያክብር፤ ለመጻተኛና ለአገሩ ተወላጅ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑራችሁ።”


በዚያ ዘመን በዚህም ዓለም ያለ ክርስቶስ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፥ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፥ ተስፋን አጥታችሁና ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።


አንድ እግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘በግብጽ በፈርዖን ቤት ባርያ ሳሉ ለአባትህ ቤት ተገለጥሁ፤


跟着我们:

广告


广告