Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የቤተሰቡ ቍጥር ም ለጠቦቱ የሚያንስ ከሆነ እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ በእያንዳንዱ ሰው ቍጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ፤ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ማንኛውም ቤተ ሰብ ለአንድ ሙሉ ጠቦት ቍጥሩ አነስተኛ ከሆነ፣ በጎረቤት ያሉትን ሰዎች ቍጥር እስከ ቅርብ ከሆነው ጋራ መካፈል ይኖርበታል፤ እያንዳንዱ ሰው በሚበላው መጠንም ምን ያህል ጠቦት እንደሚያስፈልግ መወሰን ይኖርባችኋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ቤተሰቡ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሣ እንስሳውን በልቶ ለመጨረስ የማይችል ከሆነ ግን እርሱና የቅርብ ጐረቤቱ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ሊመገበው የሚችለውን ያኽል ተመጥኖ እንስሳውን በአንድነት አብረው ይብሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በቤት ያሉት ሰዎች ጥቂት ቢሆኑ፥ አንድ በግም የማ​ይ​ጨ​ርሱ ቢሆኑ በጉን ሊጨ​ርሱ በሚ​በቁ በሰ​ዎች ቍጥር እያ​ን​ዳ​ንዱ በአ​ጠ​ገቡ የሚ​ኖ​ረ​ውን ጎረ​ቤ​ቱን ይው​ሰድ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የቤቱ ሰዎች ቁጥርም ጠቦቱን ለመጨረስ የማይበቃ ቢሆን እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ እንደ ነፍሶቻቸው ቁጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ፤ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 12:4
4 交叉引用  

ባርዚላይ ግን ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የምሄደው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ ነው?


ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ። በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት፥ ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ።


የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት፥ ተባዕት፥ የአንድ ዓመት ይሁን፤ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ።


ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ ፋሲካውንም አዘጋጁ።


跟着我们:

广告


广告