ዘፀአት 12:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 እንዲህም ሆነ እኩለ ሌሊት ላይ ጌታ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በእስር ቤት እስካሉት እስከ እስረኞች በኩር ድረስ፥ የከብቶችንም በኩር ሁሉ መታ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም29 እኩለ ሌሊት ላይ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኵር ልጅ ጀምሮ፣ በጨለማ እስር ቤት ውስጥ እስካለው እስረኛ የበኵር ልጅ ድረስ ያለውንና የእንስሳቱን በኵሮች ሁሉ ቀሠፋቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 እኩለ ሌሊት ሲሆን እግዚአብሔር ከንጉሡ አልጋ ወራሽ ጀምሮ ከምድር በታች ባለ እስር ቤት ውስጥ እስከ ተጣለው የእስረኛ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነውን ወንድ ልጅ ሁሉ በሞት ቀጣ፤ በኲር ሆነው የተወለዱ እንስሶችም ተገደሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 እንዲህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምርኮኛ በኵር ድረስ፥ በግብፅ ምድር በኵሩን ሁሉ፥ የእንስሳውንም በኵር ሁሉ መታ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 እንዲህም ሆነ፤ እኩል ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በግዞት እስካሉት እስከ ምርኮኞቹ በኵር ድረስ፥ የግብፃውያንን በግብፅ ምድር የተገኘውን በኵር ሁሉ፥ የእንስሳውንም በኵሮች ሁሉ መታ። 参见章节 |