Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የግብጽም ንጉስ አዋላጆቹን ጠርቶ፦ “ለምን ይህን አደረጋችሁ? ወንዶቹን ሕፃናትንስ ለምን በሕይወት እንዲኖሩ ፈቀዳችሁላቸው?” አላቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ንጉሡም አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምንድን ነው ወንዶቹን ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ የተዋችኋቸው?” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህ በኋላ የግብጽ ንጉሥ አዋላጆቹን አስጠርቶ “ወንዶች ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ያደረጋችኹበት ምክንያት ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የግ​ብ​ፅም ንጉሥ አዋ​ላ​ጆ​ችን ጠርቶ፥ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ጋ​ችሁ? ወን​ዶ​ቹን ሕፃ​ና​ት​ንስ ለምን አዳ​ና​ችሁ?” አላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የግብፅም ንጉስ አዋ“ላጆችን ጠርቶ፦ “ለምን እንዲህ አደረጋችሁ?” ወንዶቹን ሕፃናትንስ ለምን አዳናችሁ?” አላቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 1:18
4 交叉引用  

ከዚያም አቤሴሎም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ መንፈሱ መለወጡን ተጠባበቁ፤ እኔ ‘አምኖንን፥ ምቱት’ በምላችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ያዘዝኋችሁ እኔው ስለሆንኩ አትፍሩ፤ ብርቱዎች ሁኑ፥ ጨከን በሉም” ብሎ አዘዛቸው።


አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፥ የግብጽ ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፥ ወንዶቹን ሕፃናትንም በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ተዋቸው።


አዋላጆቹም ፈርዖንን፦ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብጽ ሴቶች አይደሉም፤ እነርሱ ጠንካሮች ናቸውና አዋላጆች ሳይገቡ ስለሚወልዱ ነው” አሉት።


የንጉሥ ቃል ኃይለኛ ነውና፥ “ይህንስ ለምን ታደርጋለህ?” ማን ይለዋል?


跟着我们:

广告


广告