መክብብ 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፤ መልካሙ ሰው እንደ ኃጢአተኛው፥ የሚምለው ሰው መሐላን እንደሚፈራው ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ጻድቃንና ኃጥኣን፣ ደጎችና ክፉዎች፣ ንጹሓንና ርኩሳን፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የማያቀርቡ፣ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። ለደጉ ሰው እንደ ሆነው ሁሉ፣ ለኀጢአተኛውም እንዲሁ ነው፤ ለሚምሉት እንደ ሆነው ሁሉ፣ መሐላን ለሚፈሩትም እንዲሁ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ምንም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግ ለጻድቅና ለኃጢአተኛ ለደግና ለክፉ፥ ለንጹሓንና ንጹሓን ላልሆኑ መሥዋዕት ለሚያቀርቡትና ለማያቀርቡትም የሚገጥማቸው ዕድል አንድ ዐይነት ነው፤ ይኸውም ደጉ ሰው ከኃጢአተኛው የተሻለ ዕድል የለውም፤ መሐላን የሚፈራው መሐላን ከሚደፍረው ሰው ተለይቶ አይታይም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በሁሉም ከንቱነት አለ፥ የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የመልካሙና እንዲሁ የኀጢአተኛው፥ የመሐላኛውና እንዲሁ መሐላን የሚፈራው ድርሻ አንድ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፥ እንደ መልካሙ ሰው እንዲሁ ኃጢአተኛው፥ እንደ መሐለኛው ሰው እንዲሁ መሐላን የሚፈራው ነው። 参见章节 |