Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንግዲህ ሰው ልጁን እንደሚገሥፅ፥ እንዲሁም ጌታ እግዚአብሔር አንተን እንደሚገሥጽህ በልብህ አስተውል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ሰው ልጁን እንደሚቀጣ፣ አምላክህ እግዚአብሔርም አንተን እንደሚቀጣህ በልብህ ዕወቅ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አባት ልጆቹን እንደሚገሥጽ አምላክህ እግዚአብሔርም አንተን የሚገሥጽህ መሆኑን አስተውል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሰውም ልጁን እን​ደ​ሚ​ገ​ሥጽ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን እን​ዲ​ገ​ሥጽ በል​ብህ ዕወቅ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሰውም ልጁን እንደሚገሥፅ እንዲሁም አምላክህ እግዚአብሔር አንተን እንዲገሥጽ በልብህ አስተውል።

参见章节 复制




ዘዳግም 8:5
19 交叉引用  

አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል በሚፈጽምበትም ጊዜ ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።


ሥርዓቴንም ቢያረክሱ፥ ትእዛዜንም ባይጠብቁ፥


ለክፉ ሰው ጉድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከአስከፊ ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።


በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፥ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።


ልጄ ሆይ፥ የጌታን ተግሣጽ አትናቅ፥ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር።


ጌታ የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ።


በመልካም ቀን ደስ ይበልህ፥ በክፉም ቀን ተመልከት፥ ሰው ከእርሱ በኋላ መርምሮ ምንም እንዳያገኝ እግዚአብሔር ይህንንም ያንንም እንዲሁ ሠርቶአል።


በሬ ጌታውን፤ አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤ እስራኤል ግን አላወቀም፤ ሕዝቤም አላስተዋለም።”


አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የስደተኛ ጓዝ ለራስህ አዘጋጅ፥ እያዩህም በቀን ወደ ምርኮ ሂድ፥ በፊታቸውም እንደ ምርኮኛ ከስፍራህ ወደ ሌላ ስፍራ ሂድ፥ ዓመፀኛ ቤት ቢሆኑም ምናልባት ያስተውሉ ይሆናል።


የሠራውን በደል ሁሉ አይቶ ተመልሶአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።


ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን።


ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ በምድረ በዳም፥ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ፥ ጌታ አምላካችሁ እንዴት እንደተንከባከባችሁ አይታችኋል።’


ጌታ አምላካችሁ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ ጌታ አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም መልክ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።


ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳቱን አሳያችሁ፥ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።።


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


እርሱን በመፍራትና የእርሱንም መንገድ በመከተል፥ የጌታ የአምላክህን ትእዛዞች ጠብቅ።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ተነሣሣ፤ ንስሓም ግባ።


跟着我们:

广告


广告