Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 8:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 መርዘኛ እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከዓለት ድንጋይም ውኃን ያፈለቀልህን፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በዚያ ጭልጥ ባለና አስፈሪ ምድረ በዳ፣ በዚያ በሚያስጠማና ውሃ በማይገኝበት ደረቅ መሬት፣ መርዘኛ እባብና ጊንጥ ባለበት ምድረ በዳ መራህ፤ ከጽኑ ዐለትም ውሃ አፈለቀልህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 መርዘኛ እባብና ጊንጥ በሞላበት፥ አስፈሪ በሆነው በዚያ ሰፊ በረሓ መርቶሃል፤ ምንም ውሃ በማይገኝበት ደረቅ በረሓ ከጽኑ አለት ውሃን አፈለቀልህ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የሚ​ና​ደፍ እባ​ብና ጊንጥ፥ ጥማ​ትም ባለ​ባት፥ ውኃም በሌ​ለ​ባት፥ በታ​ላ​ቂ​ቱና በም​ታ​ስ​ፈ​ራው ምድረ በዳ የመ​ራ​ህን፥ ከጭ​ንጫ ድን​ጋ​ይም ጣፋጭ ውኃን ያወ​ጣ​ል​ህን፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እባብና ጊንጥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት፥ በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከጭንጫ ድንጋይም ውኃን ያወጣልህን፥

参见章节 复制




ዘዳግም 8:15
16 交叉引用  

ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈለቀ፥ ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ፥


ዐለቱን ወደ ውኃ መቆሚያ፥ ድንጋዩንም ወደ ውኃ ምንጭ ይለውጣል።


ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።


ደረቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተጠማች መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ለምለም፥ ሸምበቆው ደንገል ይበቅልበታል።


እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ።


እነርሱም፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጉድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም።


በምድረ በዳ፥ እጅግ በደረቀ ምድር አውቄህ ነበር።


ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ።


ጌታም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ላከ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ።


ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዐለት ነበር፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።


“ከኮሬብም ወጣን፥ ጌታ አምላካችን እንዳዘዘን በታላቁ እጅግም በሚያስፈራ በዚያ ሁሉ ባያችሁት ምድረ በዳ በኩል በተራራማው በአሞራውያን መንገድ ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።


“በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፥ የምድሩንም ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ ማር፥ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው።


跟着我们:

广告


广告