Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 4:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ፥ ከእናንተ የበረቱትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊታችሁ እንዲያስወጣ፥ እናንተንም እንዲያስገባ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ይሰጣችሁ ዘንድ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ከፊትህ በማስወጣት ወደ ምድራቸው አስገብቶህ ለአንተ ርስት አድርጎ ለመስጠት ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ይህንንም ማድረጉ ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ከእናንተ የሚበልጡትንና ኀያላን የሆኑትን ሕዝቦች አስወጥቶ ምድራቸውን ለእናንተ ርስት ለማድረግ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግ​ብፅ ከአ​ንተ የጸ​ኑ​ትን ታላ​ላ​ቆ​ቹን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አን​ተ​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ባህ፥ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ርስት አድ​ርጎ እን​ዲ​ሰ​ጥህ፥

参见章节 复制




ዘዳግም 4:38
14 交叉引用  

እነሆ፥ ለበጎነታችን ክፋት ይመልሱልናል፤ ከሰጠኸንም ርስት ሊያወጡን መጥተዋል።


አምላካችን ሆይ! በዚህ ምድር የነበሩትን አሕዛብ ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት ያሳደድህ፥ ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘለዓለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን?


ጌታ የእስራኤል ማኅበር እንዲወርሰው ያደረገው ምድር ሲሆን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባርያዎችህ እንስሶች አሉን።”


የሮቤልም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የጋድም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ወርሰዋል።


እነዚህ ሁለቱ ነገድና የአንዱ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ አንጻር በስተ ምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ወረሱ።”


ከዚያም ጌታ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፥ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ።


“ጌታም፦ ‘ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት፥ እነሆ፥ ጀመርሁ፤ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር’ አለኝ።”


“ጌታ አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ፥ ከአንተ የበለጡትን እና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ፥ ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን ባስወጣልህ ጊዜ፥


ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።


ኢያሱም እንዲህ አለ፦ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደሆነ፥ እርሱም ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈፅሞ እንደሚያሳድድ በዚህ ታውቃላችሁ።


跟着我们:

广告


广告