Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “ጌታ በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ ምንም መልክ አላያችሁምና፥ ለነፍሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግዚአብሔር በኮሬብ ተራራ ላይ በእሳት ውስጥ በተናገራችሁ ቀን ምንም ዐይነት መልክ ከቶ አላያችሁም፤ ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “በሲና ተራራ ከእሳቱ ነበልባል መካከል እግዚአብሔር በአነጋገራችሁ ጊዜ ምንም ያያችሁት መልክ አልነበረም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ተራራ በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ በተ​ና​ገ​ራ​ችሁ ቀን መል​ኩን ከቶ አላ​ያ​ች​ሁ​ምና ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን እጅግ ጠብቁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤

参见章节 复制




ዘዳግም 4:15
22 交叉引用  

ከምድሪቱም ነውጥ በኋላ እሳት መጣ፤ ጌታ ግን በእሳት ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም በኋላ የሹክሹክታ ድምፅ ተሰማ።


ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።


የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር በወጡ በሦስተኛው ወር በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።


በላይ በሰማያት ካለው፥ በታች በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም አምሳል፥ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ።


ከሁሉ አስበልጠህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት ምንጭ እርሱ ነውና።


ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፥ እግርህንም ከክፉ መልስ።


እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፥ በሰንበትም ቀን ሸክም አትሸከሙ፥ በኢየሩሳሌምም በሮች አታስገቡ፥


አንድ አላደረጋቸውምን? የመንፈስም ቅሪት ለእርሱ ነው? አንዱስ ምን ፈልጎ ነው? የእግዚአብሔርን ዘር ፈልጎ ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።


ዐሥርቱን ቃላት ጌታ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገራችሁ ተሰብስባችሁበት በነበረበት ቀን፥ ቀድሞ ተጽፈው እንደነበረው በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፥ እነርሱንም ጌታ ለእኔ ሰጠኝ።


ጌታም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ የቃሉን ድምፅ ሰማችሁ፥ ድምፅን ብቻ ነበር እንጂ መልክ አላያችሁም።


ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር የምታደርጉትን ሥርዓትና ሕግጋት እንዳስተምራችሁ ጌታ በዚያን ጊዜ አዘዘኝ።


ጌታ አምላካችሁ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፥ ጌታ አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም መልክ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።


ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳቱን አሳያችሁ፥ ከእሳቱም መካከል የእርሱን ድምፅ ሰማችሁ።።


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ጌታ ፊት ለፊት አናገራችሁ።


“ ‘በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፥


ጌታም በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፥ ተሰብስባችሁ በነበረበትም ቀን ጌታ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የነገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።


እርሱም የክብሩ ጸዳልና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኀጢአታችንን ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤


ጌታን አምላካችሁንም የምትወድዱ መሆናችሁን እጅግ በጥንቃቄ አስተውሉ።


跟着我们:

广告


广告