Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 33:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከፀሐዩ ሙቀት ከሚገኘው ምርጥ ፍሬ፥ ከወራት መፈራረቅ ከሚገኘው ምርት፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ፀሓይ በምታስገኘው ምርጥ ፍሬ፣ ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም ምርት፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እንዲሁም በፀሐይ በበሰለ ምርጥ ፍሬ የተመላ ይሁን፤ በየወቅቱም ብዙ ምርት ይስጥ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከፀ​ሐይ መው​ጣት ከሚ​ገ​ኘው ፍሬ፥ በወ​ራት ቍጥር ከሚ​ገ​ኘው ምርት፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በፀሐዩ ፍሬያት ገናንነት፥ 2 በጨረቃውም መውጣት ገናንነት

参见章节 复制




ዘዳግም 33:14
15 交叉引用  

እርሱ፥ እንደ ንጋት ብርሃን እንደ ማለዳ ፀሐይ አወጣጥ፥ ደመና በሌለበት ማለዳ እንደምታበራ የብርሃን ጸዳል፥ ከዝናብ በኋላ ከምድር እንደሚበቅል ልምላሜ ይሆናል።


ወቅቶችን ለማመልከት ጨረቃን አደረግህ፥ ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።


ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፥ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።


በጠላቶችህ ምክንያት ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።


ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።


ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፥ ምድሪቱም የተትረፈረፈ ምርትዋን ትሰጣለች፥ የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።


ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ ከጋጣ እንደ ወጡ ጥጃዎች ትቦርቃላችሁ።


ይህን በማድረግ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው፤ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣልና፥ ለጻድቃንና ለኃጥኣንም ዝናቡን ያዘንባልና።


ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም።”


“ጌታ በጐተራህና እጅህ በነካው ሁሉ ላይ በረከቱን ይልካል። ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ላይ ይባርክሃል።


ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ “ምድሩ ከጌታ ዘንድ የተባረከ ይሁን፤ ከሰማያት በሚዘንበው የላቀ ስጦታ፥ ከታችም ከጥልቀት ከሚገኘው ውሃ፥


ከቀደሙትም ከጥንት ተራሮች ከፍተኛነት፥ በዘለዓለሙም ኮረብቶች ገናንነት፥


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።


በከተማው አደባባይዋም መካከል፥ በወንዙም ወዲያና ወዲህ፥ በየወሩ እያፈራ ዐሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝቦች መፈወሻ ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告