Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 3:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ይልቅስ ኢያሱን እዘዘው፥ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፥ አንተም የምታያትን ምድር እርሱ ያወርሳቸዋልና፥ አደፋፍረውም፥ አበርታውም።’

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ነገር ግን ሕዝቡን መርቶ በማሻገር የምታያትን ምድር እንዲወርሱ የሚያደርጋቸው ስለ ሆነ፣ ኢያሱን ላከው፤ አደፋፍረው፤ አበረታታውም።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ይልቅስ ለኢያሱ አስፈላጊውን መመሪያ ስጠው፤ በማበረታታትም አጠንክረው፤ ሕዝቡ ተሻግረው ይህችን የምታያትን ምድር ይወርሱ ዘንድ የሚመራቸው እርሱ ነው።’

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻ​ገ​ራ​ልና፥ አን​ተም የም​ታ​ያ​ትን ምድር እርሱ ያወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ልና ኢያ​ሱን እዘ​ዘው፤ አደ​ፋ​ፍ​ረ​ውም፥ አጽ​ና​ውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፥ አንተም የምታያትን ምድር እርሱ ያወርሳቸዋልና ኢያሱን እዘዘው፥ አደፋፍረውም፥ አጽናውም።

参见章节 复制




ዘዳግም 3:28
18 交叉引用  

ልጁንም ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ስም ቤት እንዲሠራ አዘዘው።


ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፦ “ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፥ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።


ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።


አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።


በእናንተው ምክንያት ጌታ በእኔም ላይ ደግሞ ተቆጥቶ እንዲህም አለኝ፤ ‘አንተም ደግሞ ወደዚያ አትገባም፤


በፊትህ የሚቆመው የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደዚያ ይገባል፤ እርሱ ለእስራኤል ምድሪቱን ያወርሳልና አበረታታው።’


ጌታም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ፥ “በርታ፤ ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገ ባቸዋለህና፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” በማለት ትእዛዝ ሰጠው።


ጌታ አምላክህም ራሱ በፊትህ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ አንተም ምድራቸውን ትወርሳለህ፤ ጌታ እንደ ተናገረው ኢያሱም አንተን ቀድሞ ይሻገራል።


ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት እንዲህ አለው፤ “ጌታም ለአባቶቻቸው ሊሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ከዚህ ሕዝብ ጋር አብረህ ስለምትገባ፥ ምድሪቱን ርስታቸው አድርገህ ስለምታከፋፍል በርታ፤ ደፋርም ሁን።


ኢያሱ አሳርፎአቸው ኖሮ ቢሆንስ፥ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር።


“ባርያዬ ሙሴ ሞቷል፤ እንግዲህ አሁን አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።


跟着我们:

广告


广告