Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያን ወቅት ይህችን ምድር በወረስን ጊዜ፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠኋቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚያ ጊዜ ከያዝነው ምድር ላይ በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር አንሥቶ በስተሰሜን ያለውን ግዛት፣ በተጨማሪም ኰረብታማውን የገለዓድ አገር እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “ምድሪቱን ከወረስን በኋላ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከዓሮዔር ከተማ ጀምሮ በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ግዛትና የኮረብታማይቱን የገለዓድን እኩሌታ ከነከተሞችዋ ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ይህ​ች​ንም ምድር በዚ​ያን ዘመን ወረ​ስን፤ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን ተራ​ራማ ሀገር እኩ​ሌታ፥ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ ነገድ ሰጠ​ኋ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይህችንም ምድር በዚያን ዘመን ወረስን፤ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገድ ሰጠኋቸው።

参见章节 复制




ዘዳግም 3:12
10 交叉引用  

እርሱም የያዘው ግዛት፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ፥ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ አሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ፥ የሮቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል።


ሙሴም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠ፤ እርሱም በእርሷ ተቀመጠ።


በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።


ወደዚህም ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ፥ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ነገር ግን ድል አደረግናቸው።


ምድራቸውንም ወርሰን ለሮቤላውያን፥ ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን።


ከገለዓድም የቀረውን የዖግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ግዛት ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፥ ያቺ ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተጠራች።


በአርኖን ወንዝ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ እስከ ሲሪዮን ተራራ፥ ይህም ሔርሞን ድረስ፥


跟着我们:

广告


广告