Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 29:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር ጌታ እንደሆንኩ እንድታውቁ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ቂጣ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቁ ዘንድ እንጀራ አልበላችሁም ወይን ወይም ጠንካራ መጠጥ አልጠጣችሁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እዚህ ቦታ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ድረስ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ች​ሁም፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ውን መጠ​ጥም አል​ጠ​ጣ​ች​ሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ እንጀራ አልበላችሁም፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክረውን መጠጥ አልጠጣችሁም።

参见章节 复制




ዘዳግም 29:6
14 交叉引用  

ለረኃባቸው ከሰማይ ምግብ ሰጠሃቸው፥ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃ አፈለቅህላቸው፤ ልትሰጣቸው ወደ ማልክላቸው ምድር ገብተው እንዲወርሱ ነገርካቸው።”


የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረማቸውን ሰማሁ፦ እንዲህ በላቸው “ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።”


የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ።


ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላስገባኸንም፥ እርሻና የወይንም ተክል ቦታ አላወረስከንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም።”


“በትሩን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ እነርሱም ዓይናቸው እያየ ድንጋዩ ውኃን እንዲሰጥ ተናገሩት፤ ለእነርሱም ከድንጋዩ ውኃ ታወጣላቸዋለህ፤ እንዲሁም ለማኅበሩና ለከብቶቻቸው የሚጠጣ ወኃ ትሰጣቸዋለህ።”


ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዐለት ነበር፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።


የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ራሱን መግዛት ይለማመዳል፤ እነርሱ ጠፊውን አክሊል፤ እኛ ግን የማይጠፋውን፥ ለማግኘት ነው።


መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ ብክነት እንደ ሆነው በወይን ጠጅ አትስከሩ፤


ጌታ አምላካችንም እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን።


ወደዚህም ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ፥ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ነገር ግን ድል አደረግናቸው።


ስለዚህ ጌታ አምላካችን ደግሞ የባሳንን ንጉሥ ዖግን ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፥ እኛም አንድ ሰው እንኳ ሳናስቀርለት አጠፋነው።


በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ ደመሰስናቸው፥ እያንዳንዱን ከተማ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችና ሕፃናት ሁሉ አጠፋናቸው።


ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከጌታ አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ሊያሳውቅህ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።


跟着我们:

广告


广告