Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 28:55 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ታህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ምክንያቱም ከተሞችህ ሁሉ ጠላቶችህ ከበው ከሚያደርሱብህ ሥቃይ የተነሣ ከዚህ በቀር የተረፈው የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ታኽል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ከተሞችህ ሁሉ በመከበባቸው ጠላቶችህ ከሚያደርሱብህ ሥቃይ የተነሣ ለርሱ የቀረለት ይህ ብቻ ነውና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 በዚያ ተስፋ በሚያስቈርጠው በከተሞችህ ሁሉ ላይ በሚደረገው በጠላት ከበባ ወቅት ሌላ ምንም የሚበላው ነገር ስለሌለው ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለማናቸውም አይሰጥም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ውስጥ ጠላ​ቶ​ችህ ከብ​በው ባስ​ጨ​ነ​ቁ​ህና መከራ ባሳ​ዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀ​ረው የለ​ምና ከሚ​በ​ላው ከል​ጆቹ ሥጋ ለአ​ንዱ አይ​ሰ​ጥም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም።

参见章节 复制




ዘዳግም 28:55
7 交叉引用  

የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፥ ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና ከበባ ሁሉም የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።’


“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሂድ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር እንዲህም በለው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ በእሳትም ያቃጥላታል፤


“በወይኗ ትልሞች በመካከል ሂዱና አበላሹ፥ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የጌታ አይደሉምና ቅርንጫፍዋን ውሰዱ።


በአራተኛውም ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር፥ ለአገሬውም ሰው እንጀራ ታጣ።


“ጠላቶችህ ከበው በሚያስጨንቁህ ጊዜ፥ ከሥቃይ የተነሣ፥ ጌታ እግዚአብሔር የሰጠህን፥ የሆድህ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።


በመካከልህ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ፥ አቅፋውም ለምትተኛ ለሚስቱ፥ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይሳሳም።


በመካከልህ ተለሳልሳና ተቀማጥላ የምትኖር፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሮችዋ ዐፈር ነክቶት የማያውቁ ሴት ዐቅፋው ለምትተኛው ባሏና በገዛ ወንድ ወይም ሴት ልጆችዋ ላይ ትከፋለች።


跟着我们:

广告


广告