Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 26:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከዚያ በኋላ ለጌታህ እግዚአብሔር እንዲህ በል፦ ‘ከቤቴ የተቀደሰውን ድርሻ ወስጄ በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያ በኋላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲህ በል፤ “በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት የተቀደሰውን ክፍል ከቤቴ አውጥቼ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚያም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ በል፦ ‘ከቤቴ የተቀደሰውን ድርሻ ወስጄ ባዘዝከን ትእዛዞች ሁሉ መሠረት ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥቼአለሁ፤ ከትእዛዞችህም አልተላለፍኩም፤ የዘነጋሁትም ነገር የለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ በል፦ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር ከቤቴ ለይች ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሀ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸኝ ትእ​ዛዝ ሁሉ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ምንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ሁም፤ አል​ረ​ሳ​ሁ​ምም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ በል፦ የተቀደሰውን ነገር ከቤቴ ወስጄ ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድሀ አደጉም ለመበለቲቱም እንዳዘዝኽኝ ትእዛዝ ሁሉ ሰጥቼአለሁ፤ ትእዛዝህን ምንም አላፈረስሁም፥ አልረሳሁምም፤

参见章节 复制




ዘዳግም 26:13
19 交叉引用  

ጠላቶቼ ቃልህን ረስተዋልና የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ።


እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ፥ ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም።


ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት አድነኝም።


እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፥ ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባርያህን ፈልገው።


በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘለዓለም አልረሳም።


እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥


ልጄ ሆይ፥ ሕጌን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።


ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።


ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እንዳልዋሸሁ ያውቃል።


ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፥ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፥ አንተንም አምላክህ ጌታ በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።


“አሥራት በምታወጣት በሦስተኛው ዓመት ከምርትህ አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፥


በኀዘኔም ጊዜ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ወይም ንጹህ ባልነበርኩ ጊዜ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት መባ የለም፤ ለአምላኬ ጌታ ድምጽ ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።


በእናንተ በአማኞች መካከል እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ነበርን እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


跟着我们:

广告


广告