Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “አለቆቹም ለሠራዊቱ እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አለቆቹም ለሰራዊቱ እንዲህ ይበሉ፤ “አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ከዚህ በኋላ የጦር መሪዎች ለዘማቾች እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት የሠራና አስመርቆ ያልገባበት ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ሌላ ሰው ቤቱን አስመርቆ ይገባበታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጸሐ​ፍ​ትም ለሕ​ዝቡ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላ​ስ​መ​ረቀ ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ስ​መ​ር​ቀው ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አለቆችም ለሕዝቡ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያስመረቀው ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።

参见章节 复制




ዘዳግም 20:5
8 交叉引用  

የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲመረቅ ምረቃውን በደስታ፥ በምስጋና፥ በመዝሙር፥ በጸናጽል፥ በበገናና በክራር ለማክበር ሌዋውያኑን ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በየሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ፈለጉ።


ለቤቱ መመረቅ ምስጋና፥ የዳዊት መዝሙር።


ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጦሩ አዛዦች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ።


በብዙ ሺህ በሚቆሩት ሠራዊት ላይ የተሾሙት የጦር አዛዦች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች፥ ወደ ሙሴ ቀረቡ፥


እኔም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን አለቆች ተቀበልኩ፥ በእናንተም ላይ የሺህ አለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የኀምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም ገዢዎችም በየነገዶቻቸው አደረግኋቸው።


“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።


ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ወይኑን ሌላ ሰው ይበላዋል።


ይህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለሻለቃው የጦር አዛዥ አብረህ ውሰድ፤ ወንድሞችህም እንዴት እንደ ሆኑ አይተህ፥ ደኅንነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት ከእነርሱ ዘንድ አምጣልኝ።


跟着我们:

广告


广告