Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 18:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ሌዋውያን ካህናት፥ የሌዊ ነገድም ሁሉ ከእስራኤል ጋር የመሬት ድርሻ ወይም ርስት አይኖራቸውም፤ ድርሻቸው ነውና ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው መባ ይብሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሌዋውያን ካህናት፣ የሌዊ ነገድም ሁሉ ከእስራኤል ጋራ የመሬት ድርሻ ወይም ርስት አይኖራቸውም፤ ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው መባ ይብሉ፤ ድርሻቸው ነውና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ሌዋውያን ካህናት፥ እንዲያውም፥ መላው የሌዊ ነገድ ከቀሩት የእስራኤል ነገዶች ጋር የርስት ድርሻ የላቸውም፤ በዚህ ምትክ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕትና መባ እየተመገቡ ይኖራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “ለሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት፥ ለሌ​ዊም ነገድ ሁሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ድር​ሻና ርስት አይ​ኑ​ራ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት ድር​ሻ​ቸው ነው፤ እር​ሱን ይመ​ገ​ባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ለሌዋውያን ካህናት፥ ለሌዊም ነገድ ሁሉ ከእስራኤል ጋር ድርሻና ርስት አይሆንላቸውም፤ በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕቱንና ርስቱን ይበላሉ።

参见章节 复制




ዘዳግም 18:1
12 交叉引用  

እንዲሁም ሌዋውያን ካህናት በእኔ ፊት የሚቃጠለውን መሥዋዕት የሚያቀርብ፥ የእህሉንም ቁርባን የሚያቃጥል፥ ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ፈጽሞ አያጡም።”


ርስት ይሆንላቸዋል፤ ርስታቸው እኔ ነኝ፤ በእስራኤልም ግዛት አትስጡአቸው፤ ግዛታቸው እኔ ነኝ።


ጌታም አሮንን እንዲህ አለው፦ “በምድራቸው ርስት በመካከላቸውም ድርሻ አይኖርህም፤ በእስራኤል ልጆች መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።


ዕድሜአቸው አንድ ወር የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሀያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም።


ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ጌታ ርስቱ ነው።


በምድርም ላይ በምትኖርበት ጊዜ ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትለው ተጠንቀቅ።”


ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አልሰጠም፤ እርሱ እንደ ተናገራቸው እንዲሁ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ በእሳት የሚቀርበው መሥዋዕት ርስታቸው ነው።


ለሌዊ ነገድ ግን ሙሴ ርስት አልሰጠም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንደ ነገራቸው እንዲሁ ርስታቸው እርሱ ነው።


ነገር ግን የጌታ ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዋውያን በመካከላችሁ ድርሻ የላቸውም፤ ጋድም ሮቤልም የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የጌታ ባርያ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።”


跟着我们:

广告


广告