Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 12:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የሚቃጠል መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንም ደሙንም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በጌታ አምላክህ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የሚቃጠል መሥዋዕትህን፣ ሥጋውንም ደሙንም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን፥ ማለትም ሥጋውንና ደሙን ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ። የሌሎች መሥዋዕቶችህ ደም ከአምላክህ ከእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን ልትበላ ትችላለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ሥጋ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ፥ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ርብ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ት​ህም ደም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ላይ ይፍ​ሰስ፥ ሥጋ​ው​ንም ብላው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የሚቃጠለውንም መሥዋዕትህን፥ ሥጋውንና ደሙን፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የመሥዋዕትህም ደም በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብላው።

参见章节 复制




ዘዳግም 12:27
7 交叉引用  

የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሌላ መሥዋዕቶቻችሁ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፥ ሥጋውንም ብሉ።


የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል። ካህኑም ሁሉን ያቀርበዋል፤ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን፥ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።


በሬውንም በጌታ ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።


የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በእሳትም የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ሁሉንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።


የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ እንዲሆን እኔ ለእናንተ ሰጠሁት።


“ቁርባኑም የአንድነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከበሬ መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በጌታ ፊት ያቅርብ።


ካህኑም ከደምዋ በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ የተረፈውንም ደምዋን ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሳል።


跟着我们:

广告


广告