Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ጌታ አምላካችን በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ ‘በዚህ ተራራ ለረጅም ጊዜ ቆይታችኋል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔር አምላካችን በኮሬብ እንዲህ አለን፤ “እነሆ፤ በዚህ ተራራ ለረዥም ጊዜ ቈይታችኋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “በሲና ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን እንዲህ አለን፦ ‘እነሆ፦ በዚህ ተራራ ላይ ለረጅም ጊዜ ቈይታችኋል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረን፦ በዚህ ተራራ መቀ​መ​ጣ​ችሁ በቃ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ በዚህ ተራራ የተቀመጣችሁት በቃ፤

参见章节 复制




ዘዳግም 1:6
9 交叉引用  

እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ከእርሱ ውኃ ይወጣል፥ ሕዝቡም ከእርሱ ይጠጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ።


ሙሴም የምድያን ካህን የሆነውን የአማቹን የይትሮን በጎች ያሰማራ ነበር፤ በጎቹን ከምድረ በዳው ማዶ ነዳቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


ደመናውም ሁለት ቀን ወይም አንድ ወር ወይም ረጅም ጊዜ ቆይቶ በማደሪያው ላይ ቢቀመጥ የእስራኤል ልጆች በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር፤ ነገር ግን በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር።


በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ምድር ሙሴ እንዲህ ብሎ ይህን ሕግ ይገልጥ ጀመር፦


በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፥ ‘እንዳልሞት የጌታ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ’ ብለህ አምላክህን ጌታን የጠየቅኸው ይህን ነውና።


ጌታ አምላካችን በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።


በኮሬብም የጌታን ቁጣ ቀሰቀሳችሁ፥ ጌታም ሊያጠፋችሁ እስኪነሳ አስቆጣችሁት።


跟着我们:

广告


广告