Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ቈላስይስ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም አይተውት ስለማያውቁት ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል እንደምጋደል እንድታውቁ እወዳለሁና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት እንዲሁም በአካል አይተውኝ ስለማያውቁ ሁሉ ምን ያህል እየተጋደልሁ እንደ ሆነ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን እንኳ አይተውት ስለማያውቁ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ብርቱ ትግል እንደማደርግ ልታውቁ እወዳለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም በሥጋ ስላላዩት ሁሉ እንዴት ያለ ትልቅ መጋደል እንዳለኝ ልታውቁ እወዳለሁና፤

参见章节 复制




ቈላስይስ 2:1
18 交叉引用  

ራሔልም፦ ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች፥ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።


በስቃይ ጣር ውስጥ ሆኖ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም ወደ መሬት እንደሚንጠባጠቡ የደም ጠብታዎች ሆኑ።


አሁንም እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ።


ይልቁንም “ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም፤” ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።


ልጆቼ ሆይ! ክርስቶስ በእናንተ እስኪቀረጽ ድረስ ስለ እናንተ እንደገና ምጥ ይዞኛል።


በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንደሆነ የምትሰሙት፥ ያው መጋደል ደርሶባችኋልና።


አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ አካሉም ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ካለፈባቸው መከራዎች መካከል የጐደሉትን በሥጋዬ እፈጽማለሁ።


ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ ውስጥ በኃይል በሚያቀጣጥለው ጉልበት ሁሉ እየተጋደልሁ እደክማለሁ።


በአካል ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፤ መልካሙንም ሥነ ሥርዓታችሁንና በክርስቶስም ላይ ያላችሁን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።


ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራንና እንግልትን ብንቀበልም እንኳ፥ በታላቅም ተቃውሞ ፊት የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለእናንተ ለመናገር በአምላካችን ድፍረትን አገኘን።


እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩትም በእርሱ በማመናችሁ መግለጽ በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ብሎአችኋል።


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም ላክ፤ አለኝ።”


跟着我们:

广告


广告