Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣ ዐድኜ፣ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤ እይዛቸዋለሁም። በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣ በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዝዘዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ወጥተው ቢሸሸጉም ተከታትዬ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ ወደ ጥልቅ ባሕር ገብተው ከእኔ ለመሰወር ቢሞክሩም እንዲነድፋቸው የባሕሩን ዘንዶ አዛለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በቀ​ር​ሜ​ሎስ ራስ ውስጥ ቢሸ​ሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐ​ይኔ ቢደ​በቁ በዚያ እባ​ቡን አዝ​ዛ​ለሁ፤ እር​ሱም ይነ​ድ​ፋ​ቸ​ዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በቀርሜሎስም ራስ ውስጥ ቢሸሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፥ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፥

参见章节 复制




አሞጽ 9:3
10 交叉引用  

ቀኑ በመሸ ጊዜ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፥ አዳምና ሚስቱ ከጌታ እግዚእብሔር ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።


ባዕዳን ፈሩ፤ ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።


አንተም፦ “እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?


ክፋትን የሚሠሩ የሚደበቁበት ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም።


ጌታ እንዲህ አለ፦ ከባሳን አመጣቸዋለሁ፥ ከባሕርም ጥልቅ እመልሳቸዋለሁ፥


በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።


“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥ ይላል ጌታ፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እልካለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል።


እንዲህም አለ፦ “ጌታ በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ድምፁን ያስተጋባል፤ የእረኞችም ማሰማርያዎች ይጠወልጋሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”


跟着我们:

广告


广告