Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አሞጽ 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ነገር ግን ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ዳግመኛ ትንቢት አትናገር።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤ የንጉሡ መቅደስ፣ የመንግሥቱም መኖሪያ ነውና።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ቤትኤል ግን የንጉሡ መስገጃና የሕዝቡም ቤተ መቅደስ ስለ ሆነች በዚህች ቦታ ዳግመኛ ትንቢት እንዳትናገር።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በዚያም ትንቢትን ተናገር፥ ነገር ግን ቤቴል የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትንቢት አትናገር አለው።

参见章节 复制




አሞጽ 7:13
14 交叉引用  

ከዚህም በኋላ ከወርቅ የተሠሩት ሁለት የኰርማ ምስሎች አንዱን በቤትኤል፥ ሁለተኛውንም በዳን አቆመ።


ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዓይነት ስምንተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራቸውም ምስሎች በቤትኤል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃው ምስል መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚያም በቤትኤል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ።


ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ በጌታ ትእዛዝ የተላከ አንድ ነቢይ እነሆ ከይሁዳ መጥቶ እዚያ ደረሰ፤


ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።


ባለ ራእዮችን፦ “አትመልከቱ” ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ “ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤


በጌታ ስም፦ ‘ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፥ ይህችም ከተማ ባድማና ሰው የማይኖርባ ትሆናለች’ ብለህ ስለምን ትንቢት ተናገርህ?” ብለው ያዙት። ሕዝቡም ሁሉ በጌታ ቤት ውስጥ በኤርምያስ ላይ ተሰበሰቡ።


እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችሁ፤ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ፥ ብላችሁ አዘዛችሁ።


“እስራኤልን ስለ ኃጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፤ የመሠዊያውም ቀንዶች ይሰበራሉ፥ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።


ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም ከንቱ ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፥ ወደ ጌልገላም አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።”


“አሁን ደግሞ የጌታን ቃል ስማ፤ አንተ፦ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ አልህ፤


የይስሐቅም የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፥ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ።”


ሊቀ ካህናቱም “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ፤” ብሎ ጠየቃቸው።


ሰሙትም፤ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፤ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።


跟着我们:

广告


广告