Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 7:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ነገር ግን አርባ ዓመት ሲሞላው ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ይጐበኝ ዘንድ በልቡ አሰበ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ሙሴ አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ሊጐበኝ በልቡ ዐሰበ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ሙሴ አርባ ዓመት በሞላው ጊዜ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ለመጐብኘት ተነሣሣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “አርባ ዓመት ሲሞ​ላ​ውም ወን​ድ​ሞ​ቹን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሊጐ​በ​ኛ​ቸው በልቡ ዐሰበ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ነገር ግን አርባ ዓመት ሲሞላው ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ይጐበኝ ዘንድ በልቡ አሰበ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 7:23
18 交叉引用  

ደግሞም አንድ ልብ እንዲሰጣቸው፥ በጌታም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ትእዛዝ እንዲያደርጉ የጌታ እጅ በይሁዳ ላይ ነበረ።


በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት፥ በኤርምያስ አፍ የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፥ ይህም በመንግሥቱ ሁሉ በአዋጅና በጽሑፍ እንዲያስነግር ነው፤


እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣው የይሁዳና የብንያም የአባቶች አለቆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑም ሁሉ ለመሄድና በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት ለመሥራት ተዘጋጁ።


በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት እንዲያሳምር እንደዚህ ያለውን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥ የአባቶቻችን አምላክ ጌታ ይባረክ።


ልቡ ያነሣሣውና መንፈሱ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ ለመገናኛው ድንኳን ሥራና ለአገልግሎቱ ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ የሚሆን ለጌታ ስጦታ አመጡ።


ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።


ሙሴም ሄደ፥ ወደ አማቱ ወደ ይትሮ ተመለሰ፥ እርሱም፦ “እባክህን በግብጽ ወዳሉ ዘመዶቼ እንድመለስ እስካሁንም በሕይወት እንዳሉ ሄጄ እንዳይ ፍቀድልኝ” አለው። ይትሮም ሙሴን፦ “በሰላም ሂድ” አለው።


ፈርዖንን ባናገሩት ጊዜ ሙሴ የሰማንያ ዓመት ሰው ነበር፥ አሮንም የሰማንያ ሦስት ዓመት ሰው ነበር።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።


ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ፤” አለው።


አንዱም ሲበደል አይቶ ረዳው፤ የግብጽን ሰውም መትቶ ለተገፋው ተበቀለ።


ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤


መልካም ስጦታ ሁሉ፥ ፍጹምም በረከት ሁሉ፥ እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከላይ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ ዕቅዱን በአንድ ልብ እንዲያደርጉና መንግሥታቸውንም ለአውሬው እንዲሰጡ እግዚአብሔር በልባቸው አሳድሮአልና።


跟着我们:

广告


广告