ሐዋርያት ሥራ 27:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 በነጋም ጊዜ ምድሩን አላወቁትም፤ ነገር ግን የአሸዋ ዳር ያለውን የባሕር ሰርጥ ተመለከቱ፤ ቢቻላቸውም መርከቡን ወደዚያ ይገፉ ዘንድ ቆረጡ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም39 በነጋም ጊዜ፣ ወደ የብስ መቅረባቸውን አላወቁም ነበር፤ ነገር ግን ዳር ዳሩ አሸዋማ የሆነ የባሕር ሥርጥ አይተው፣ ቢቻላቸው መርከቡን ገፍተው ወደዚያ ለማድረስ ወሰኑ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 በነጋም ጊዜ የደረሱበትን ቦታ አላወቁትም፤ ነገር ግን የአሸዋ ዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ የሚቻል ቢሆን መርከቡን ወደዚያ በመግፋት ወደ ዳር ለማውጣት አሰቡ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 በነጋ ጊዜም ቀዛፊዎች ቦታውን አልለዩም፤ የሚሄዱበትንም አላወቁም፤ ነገር ግን ለባሕሩ አቅራቢያ የሆነውን የደሴት ተራሮች አዩ፤ መርከባቸውንም ወደ እዚያ ሊያስጠጉ ፈለጉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 በነጋም ጊዜ ምድሩን አላወቁትም፥ ነገር ግን የአሸዋ ዳር ያለውን የባሕር ስርጥ ተመለከቱ፥ ቢቻላቸውም መርከቡን ወደዚያ ይገፉ ዘንድ ቈረጡ። 参见章节 |