Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 27:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ድንጋያማም ወደ ሆነ ስፍራ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ከመርከቡ በስተ ኋላ አራት መልሕቅ አወረዱ፤ ቀንም እንዲሆን ተመኙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከቋጥኞቹም ጋራ እንዳንላተም በመፍራት፣ አራት መልሕቆች ከመርከቡ በስተኋላ ጣሉ፤ ምነው በነጋ እያሉም ይለምኑ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 መርከባችን በባሕሩ ዳር ካሉ ድንጋዮች እንዳይጋጭ ፈርተው ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቆችን ወደ ባሕሩ አወረዱ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ አልፎ ቀን እንዲመጣላቸው ይጸልዩ ጀመር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ድን​ጋ​ያማ በሆነ ቦታም እን​ዳ​ይ​ወ​ድቁ ፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ር​ከቡ በስ​ተ​ኋላ አራት መል​ሕቅ በባ​ሕሩ ላይ ጣሉ፤ ፈጥኖ እን​ዲ​ነ​ጋም ጸለዩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ድንጋያማም ወደ ሆነ ስፍራ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ከመርከቡ በስተኋላ አራት መልሕቅ አወረዱ፥ ቀንም እንዲሆን ተመኙ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 27:29
8 交叉引用  

ማለዳን ከሚጠብቁ የሌሊት ጠባቂዎች ይልቅ፥ ነፍሴ ጌታን ትጠብቃለች፥ ማለዳን ከሚጠብቁ ጠባቂዎች ይልቅ።


ወደ ላይም ካወጡአት በኋላ መርከቡን በገመድ አስታጥቀው አጸኑ፤ ስርቲስም ወደሚሉት ወደ አሸዋ እንዳይወድቁ ፈርተው ሸራውን አውርደው እንዲሁ ተነዱ።


ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት እንድንወድቅ ያስፈልገናል።


መለኪያ ገመድም ቢጥሉ ሃያ በሰው ቁመት አገኙ ጥቂትም ቆይተው ሁለተኛ ቢጥሉ ዐሥራ አምስት በሰው ቁመት አገኙ፤


መርከበኞቹም ከመርከቡ ይሸሹ ዘንድ ፈልገው ከመርከቡ በስተ ፊት መልሕቅ መጣል እንዳላቸው አመካኝተው ታንኳይቱን ወደ ባሕር ባወረዱ ጊዜ፥


ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፥ ሲነጋ፥ ‘ይመሽ ይሆን?’ ሲመሽ ደግሞ፥ ‘ይነጋ ይሆን?’ ትላለህ።


ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን፤ እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤


跟着我们:

广告


广告