Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 26:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ፈቀቅ ብለውም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው እንኳንስ ለሞት ለእስራትም የሚገባ ምንም አላደረገ፤” ብለው ተነጋገሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ወጥተውም ሲሄዱ፣ “ይህ ሰው እንኳን ለሞት፣ ለእስራት የሚያበቃው ነገር አላደረገም” ተባባሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከዚያም ወጥተው ሲሄዱ፥ “ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃው ምንም ነገር አላደረገም” ተባባሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ለብ​ቻ​ቸ​ውም ገለል ብለው እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ብለው ተነ​ጋ​ገሩ፥ “ይህ ሰው እን​ዲ​ሞት ወይም እን​ዲ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ የሠ​ራው በደል የለም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ፈቀቅ ብለውም እርስ በርሳቸው፦ “ይህ ሰው እንኳንስ ለሞት ለእስራትም የሚገባ ምንም አላደረገ ብለው ተነጋገሩ።

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 26:31
10 交叉引用  

ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ ጌታን፥ “እነሆ፥ ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ! የተሳሳትሁም እኔ ነኝ! እነዚህ በጎች ግን ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ” አለ።


አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፦ “በአምላካችን በጌታ ስም ስለ ተናገረን ይህ ሰው ሞት አይገባውም” አሉ።


ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤” አለ።


በሕጋቸውም ስለ መከራከር እንደ ከሰሱት አገኘሁ እንጂ ለሞት ወይም ለእስራት የሚያደርስ ክስ አይደለም።


ታላቅ ጩኸትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው “በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን?” ብለው ተከራከሩ።


እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፤ እርሱም ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቆረጥሁ።


እነርሱም መርምረው ለሞት የሚገባ ምክንያት ስላልነበረብኝ ሊፈቱኝ አሰቡ፤


ነገር ግን በገርነትና በአክብሮት አድርጉት፤ በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ በመንቀፍ የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ መልካም ሕሊና ይኑራችሁ።


跟着我们:

广告


广告