ሐዋርያት ሥራ 22:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 የመቶ አለቃውም በሰማ ጊዜ ወደ ሻለቃው ቀርቦ “ይህ ሰው ሮማዊ ነውና ታደርገው ዘንድ ካለህ ተጠበቅ፤” ብሎ ነገረው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 የመቶ አለቃውም ይህን ሲሰማ፣ ወደ ጦር አዛዡ ቀርቦ፣ “ምን እያደረግህ እንደ ሆነ ዐውቀሃል? ሰውየው እኮ ሮማዊ ነው” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 የመቶ አለቃው ይህን በሰማ ጊዜ ወደ አዛዡ ሄደና “ምን ልታደርግ ነው? ይህ ሰው እኮ የሮም ዜጋ ነው!” አለው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 የመቶ አለቃውም ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ሻለቃው ሄደና፥ “ይህ ሰው ሮማዊ ነው፥ የምታደርገውን ዕወቅ” ብሎ ነገረው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 የመቶ አለቃውም በሰማ ጊዜ ወደ ሻለቃው ቀርቦ፦ ይህ ሰው ሮማዊ ነውና ታደርገው ዘንድ ካለህ ተጠበቅ ብሎ ነገረው። 参见章节 |