Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 21:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ሊገድሉትም ሲፈልጉ “ኢየሩሳሌም ፈጽማ ታወከች፤” የሚል ወሬ ወደ ጭፍራው ሻለቃ ወጣ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ሊገድሉት ሲፈልጉም የኢየሩሳሌም ከተማ ፍጹም ታወከች፤ ወሬውም ለሮማ ጦር አዛዥ ደረሰው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ሰዎቹ ጳውሎስን ሊገድሉት በፈለጉ ጊዜ “የኢየሩሳሌም ከተማ በሙሉ ታውካለች” የሚል መልእክት ለሮማውያኑ ጦር አዛዥ ደረሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሊገ​ድ​ሉ​ትም ፈል​ገው ብዙ ደበ​ደ​ቡት፤ ወዲ​ያ​ውም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመ​ላዋ እንደ ታወ​ከች የሚ​ገ​ልጥ መል​እ​ክት ወደ ሻለ​ቃው ደረ​ሰ​ለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሊገድሉትም ሲፈልጉ፦ ኢየሩሳሌም ፈጽማ ታወከች የሚል ወሬ ወደ ጭፍራው ሻለቃ ወጣ፤

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 21:31
19 交叉引用  

አዶንያስና እርሱም የጠራቸው ሁሉ መብሉና መጠጡ ተፈጽሞ ሳለ ሰሙ፥ ኢዮአብም የቀንደ መለከት ጽምፅ በሰማ ጊዜ፦ “ይህ በከተማ ውስጥ ያለ የሽብር ድምፅ ምንድነው?” አለ።


ነገር ግን “በሕዝቡ መካከል ሁከት እንዳይነሣ በበዓል ቀን አይሁን” አሉ።


በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ ሰበሰቡ።


ሆኖም፥ “ሕዝቡ ዐመፅ እንዳያነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም” ይባባሉ ነበር።


ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።


እንግዲህ ወታደሮቹና አዛዣቸው፥ የአይሁድም ሎሌዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፤


በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ።


አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፤ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤


ዛሬ ስለተደረገው ‘ሁከት ነው፤’ ሲሉ እንዳይከሱን ያስፈራልና፤ ስለዚህም ስብሰባ ምላሽ መስጠት አንችልም፤ ምክንያት የለምና።” ይህንም ብሎ ጉባኤውን ፈታው።


አንተ ከዚህ ዘመን አስቀድሞ ከነፍሰ ገዳዮቹ አራቱን ሺህ ሰዎች አሸፍተህ ወደ ምድረ በዳ ያወጣህ የግብጽ ሰው አይደለህምን?” አለ።


እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።


ጳውሎስም ከመቶ አለቆች አንዱን ጠርቶ “ይህን ብላቴና ወደ ሻለቃው ውሰድ፤ የሚያወራለት ነገር አለውና፤” አለው።


ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፤” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።


መቅደስንም ደግሞ ሊያረክስ ሲሞክር ያዝነው፤ እንደ ሕጋችንም እንፈርድበት ዘንድ ወደድን።


ነገር ግን የሻለቃው ሉስዮስ መጥቶ በብዙ ኃይል ከእጃችን ወሰደው፤


በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት።


ስለዚህ አይሁድ በመቅደስ ያዙኝ፤ ሊገድሉኝም ሞከሩ።


跟着我们:

广告


广告