Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሐዋርያት ሥራ 19:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የከተማይቱም ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ! የኤፌሶን ከተማ ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ የመቅደስ ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ ሰው ማን ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 የከተማዪቱም ዋና ጸሓፊ ሕዝቡን ጸጥ አሠኝቶ እንዲህ አለ፤ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፤ የታላቋ የአርጤምስ ቤተ መቅደስና ከሰማይ የወረደው ምስሏ ጠባቂ የኤፌሶን ከተማ ሕዝብ መሆኑን የማያውቅ ማን አለ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 በመጨረሻ የከተማይቱ ዋና ጸሐፊ፥ ሕዝቡን ዝም አሰኘና እንዲህ አለ፦ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ! የኤፌሶን ከተማ ነዋሪዎች፥ የታላቂቱን አርጤሚስን ቤተ መቅደስና ከሰማይ የወረደውን ምስልዋን እንደሚጠብቁ በሁሉም ዘንድ የታወቀ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ከዚ​ህም በኋላ የከ​ተ​ማው ጸሓፊ ተነ​ሥቶ ሕዝ​ቡን ጸጥ አሰ​ኝቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኤ​ፌ​ሶን ሰዎች ሆይ፥ ስሙ፤ የኤ​ፌ​ሶን ከተማ ታላ​ቂ​ቱን አር​ጤ​ም​ስ​ንና ከሰ​ማይ የወ​ረ​ደ​ውን ጣዖ​ት​ዋን እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ የማ​ያ​ውቅ ማነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የከተማይቱም ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ፦ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፥ የኤፌሶን ከተማ ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ የመቅደስ ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ ሰው ማን ነው?

参见章节 复制




ሐዋርያት ሥራ 19:35
9 交叉引用  

እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን።


ወደ ኤፌሶንም በደረሱ ጊዜ እነዚያን ከዚያ ተዋቸው፤ ራሱ ግን ወደ ምኵራብ ገብቶ ከአይሁድ ጋር ይነጋገር ነበር።


ይህም ጳውሎስ ‘በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም፤’ ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል፤ ሰምታችሁማል።


አይሁዳዊ ግን እንደሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ “የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ።


ይህንም የሚክደው ከሌለ፥ ጸጥ እንድትሉና አንዳች በችኮላ እንዳታደርጉ ይገባል።


በዚያ ዘመን በዚህም ዓለም ያለ ክርስቶስ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፥ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፥ ተስፋን አጥታችሁና ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።


ይህም ትምህርት ኅሊናቸውን በጋለ ብረት በማቃጠል አደንዝዘው ውሸትን በሚናገሩ ግብዞች በኩል የሚሰጥ ነው፤


跟着我们:

广告


广告