Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ተሰሎንቄ 2:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህም ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ትውፊት ያዙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በአንደበታችንም ሆነ በመልእክታችን ያስተላለፍንላችሁን ትምህርት አጥብቃችሁ ያዙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ሆነ በመልእክታችን ከእኛ የተላለፈላችሁን ትምህርት አጥብቃችሁ ያዙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።

参见章节 复制




2 ተሰሎንቄ 2:15
10 交叉引用  

ወንድሞች ሆይ! ከሚለያዩትና እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም መሰናክል ከሚያደርጉ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ፤


ወንድሞች ሆይ! በሁሉ ስለምታስቡኝና እኔ ያስተላለፍኩላችሁን ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።


ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።


ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤


ስለዚህ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ደስታዬና አክሊሌ ናችሁ፤ የተወደዳችሁ ሆይ! በዚህ መንገድ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ።


ከእኛ በሚመስል መልእክት ወይም በቃል ወይም በመንፈስ፦ “የጌታ ቀን መጥቷል፤” ብላችሁ አእምሮአችሁ በቀላሉ አይናወጥ አይደንግጥም።


በዚህ መልእክት በኩል ለተላከው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ሰው በምልክት ለዩት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።


ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበሉት ትውፊት ሳይሆን ሥራን በመፍታት ከሚኖሩ ወንድሞች ሁሉ እንድትለዩ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።


እውነተኛውንም ትምህርት ለመምከርና ተቃዋሚዎቹን ለመገሠጽ እንዲችል፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።


ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱሳን ሁሉ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ እንድመክራችሁና እንድጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።


跟着我们:

广告


广告