2 ሳሙኤል 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የሳኦል ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ። ዳዊትም፥ “መፊቦሼት!” ብሎ ጠራው። እርሱም፥ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት በመጣ ጊዜ፣ አክብሮቱን ለመግለጥ ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አገልጋይህ” አለ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የሳኦል የልጅ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት በመጣ ጊዜ በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት አክብሮቱን ገለጠ። ዳዊትም “መፊቦሼት!” ሲል ጠራው። መፊቦሼትም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፌቡስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሥ ዳዊትም፥ “ሜምፌቡስቴ ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ አገልጋይህ” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጣ፥ በግምባሩም ወድቆ እጅ ነሣ፥ ዳዊትም፦ ሜምፊቦስቴ ሆይ፥ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ ባሪያህ አለ። 参见章节 |