Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 6:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱና ዐብረውት ያሉት ሰዎች ሁሉ በታቦቱ ላይ ባለው ኪሩቤል ላይ በተቀመጠው በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔርም ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ወደ ባኣላ ሄዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ከይ​ሁዳ አለ​ቆች ጋር ተነ​ሥ​ተው በኪ​ሩ​ቤል ላይ የተ​ቀ​መጠ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ በይሁዳ ካለች ከበኣል ተነሥተው በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 6:2
15 交叉引用  

በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ ሲከንፍ ታየ።


ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስክር መዝሙር።


ጌታ ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፥ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።


ታዳጊያችን፥ ስሙ የሠራዊት ጌታ ነው፥ እርሱ የእስራኤል ቅዱስ ነው።


ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዳጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።


ቂርያት-ይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን በነገሯችሁ ነገር፥ እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፥ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


ስለዚህ ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ልከው፥ በኪሩቤል መካከል በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታን የኪዳን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ከኪዳኑ ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።


ከዚያም ወደ ቂርያትይዓሪም ሰዎች መልእክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የጌታን ታቦት መልሰውልናል፤ መጥታችሁ ወደ እናንተ ውሰዱት” አሏቸው።


የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የጌታን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የጌታን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።


跟着我们:

广告


广告