2 ሳሙኤል 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በዚህ ጊዜ የበኤሮታዊው የሪሞን ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ለመሄድ ተነሡ፤ እርሱም የቀትር ጊዜ ዕረፍት ለማድረግ አልጋው ላይ ተኝቶ እያለ፥ እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በዚህ ጊዜ የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ለመሄድ ዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፣ ሙቀት ሲሆን እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የሪም ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት በመሄድ እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ እርሱም በዚያን ሰዓት የቀትር ጊዜ ዕረፍት በማድረግ ላይ ነበር፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የቤሮታዊውም የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያቡስቴ ቤት መጡ፤ እርሱም በቀትር ጊዜ በአልጋው ላይ ተኝቶ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የብኤሮታዊውም የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያቡስቴ ቤት መጡ፥ እርሱም በቀትር ጊዜ በምንጣፍ ላይ ተኝቶ ነበር። 参见章节 |