2 ሳሙኤል 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ይህ የአበኔር ንግግር እጅግ ያስቆጣው ኢያቡስቴ እንዲህ አለ፤ “እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት፥ ለወንድሞቹና ለዘመዶቹ፥ ታማኝነቴን ሳላጎድል ይሄው አለሁ፤ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ ዛሬ ግን አንተ በዚህች ሴት ትከሰኛለህን? በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝ? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 አበኔርም በኢያቡስቴ ንግግር እጅግ ስለ ተቈጣ እንዲህ አለ፤ “እኔ ለይሁዳ የምወግን የውሻ ጭንቅላት ነኝን? ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹና ለዘመዶቹ ታማኝነቴን እስከ ዛሬ ድረስ አላጓደልሁም፤ አንተንም አሳልፌ ለዳዊት አልሰጠሁም፤ አሁን ግን አንተ ከዚህች ሴት ጋራ በፈጸምሁት ነገር ትከሰኛለህን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 የኢያቡስቴ ቃል አበኔርን በጣም አስቈጣው፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ ወደ ይሁዳ ነገድ የዞርኩ የማልጠቅም ውሻ ነኝን? እኔ ለአባትህ ቤት፥ ለወንድሞቹና ለወዳጆቹ ታማኝነትን አሳይቼአለሁ፤ አንተንም ለዳዊት አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ ታዲያ፥ አንተ ስለዚህች ሴት ትወቅሰኛለህን? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አበኔርም ኢያቡስቴ እንዲህ ስላለው እጅግ ተቈጣ፤ አበኔርም እንዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹም፥ ለዘመዶቹም ቸርነት አድርጌአለሁ፤ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ አንተም ዛሬ ከዚህች ሴት ጋር ስለ ሠራሁት ኀጢአት ትከስሰኛለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 አበኔርም በኢያቡስቴ ቃል እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለ፦ እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹም ለዘመዶቹም ቸርነት አድርጌአለሁ፥ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ አንተም ዛሬ ከዚህች ሴት ጋር ስለ ሠራሁት ኃጢአት ትከስሰኛለህ፥ በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? 参见章节 |