Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 21:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ሌላ ጦርነትም፥ የቤተልሔሙ የያዒር ዓርጊምን ልጅ ኤልሐናን፥ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ በተደረገ ሌላ ጦርነትም፣ የቤተ ልሔሙ የዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን፣ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጋት ሰው የጎልያድን ወንድም ገደለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ቀጥሎም በጎብ ሌላ ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተደረገ፤ በዚህም ጊዜ የቤተልሔም ተወላጅ የሆነው የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውንና የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን ጎልያድ ተብሎ የሚጠራውን ሌላ ፍልስጥኤማዊ ገደለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ደግ​ሞም በሮም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት ሆነ፤ የቤ​ተ​ል​ሔ​ማ​ዊ​ውም የዓ​ሬ​ኦ​ር​ጌም ልጅ ኤል​ያ​ናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ የነ​በ​ረ​ውን የጌት ሰው ጎዶ​ል​ያን ገደ​ለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፥ የቤተልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 21:19
5 交叉引用  

ከሠላሳዎቹ መካከል፦ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተልሔሙ ሰው የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፥


ደግሞም በሠራዊቱ ዘንድ የነበሩት ኃያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥


ዳግመኛም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደርጎ ነበር፤ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ እጀታ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ።


ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።


跟着我们:

广告


广告