Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂውም ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጣ፤ ቀና ብሎም ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ዳዊት በከተማይቱ ውስጣዊና ውጫዊ በሮች መካከል ባለው ግልጥ ቦታ ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂው በቅጥሩ በኩል ወደ ማማው ወጥቶ ስለ ነበር ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ዳዊ​ትም በሁ​ለት በር መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ ዘበ​ኛ​ውም በቅ​ጥሩ ላይ ወዳ​ለው ወደ በሩ ሰገ​ነት ወጣ፤ ዐይ​ኑ​ንም አቅ​ንቶ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሰው አየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፥ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደበሩ ሰገነት ወጣ፥ አይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:24
10 交叉引用  

አቤሴሎምም ፈጥኖ ሸሸ። ለዘብ ጥበቃ የቆመውም ሰው ቀና ብሎ ተመለከተ፤ እነሆም፥ በኋላው ብዙ ሰዎች በተራራው ጥግ ሲመጡ አየ።


አሒማዓጽም፥ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፥ “ሩጥ!” አለው። ከዚያም አሒማዓጽ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ።


ጠባቂው ተጣራና ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም፥ “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ። ሰውየውም እየቀረበ መጣ።


ንጉሡም፥ “መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” አላቸው። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ በመቶና በሺህ እየሆነ ተሰልፎ ሲወጣ፥ ንጉሡ በቅጥሩ በር ቆሞ ነበር።


በል አሁን ተነሥተህ ውጣና አገልጋዮችህን አበረታታ፤ ባትወጣ ግን በዚች ሌሊት አንድም ሰው አብሮህ እንደማይሆን በጌታ ስም እምላለሁ፤ ይህ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከደረሰብህ ክፉ ነገር ሁሉ የባሰ መከራ ያሰከትልብሃል።”


እዚያ እንደደረሰም፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፥ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፥ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ።


跟着我们:

广告


广告