Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽም እንደገና ኢዮአብን፥ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፥ “ልጄ ሆይ፥ የምሥራቹ ሽልማት እንደማያሰጥህ እያየህ መሄድ ለምን አስፈለገህ?” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደ ገና ኢዮአብን፣ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፣ “ልጄ ሆይ፣ መሄድ ለምን አስፈለገህ? ሽልማት የሚያሰጥህ ምን የምሥራች ይዘህ ነው?” ብሎ መለሰለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዳግ​መ​ኛም የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ኢዮ​አ​ብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከ​ትዬ፥ እባ​ክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮ​አ​ብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮ​ጣ​ለህ? ተመ​ለስ፤ ብት​ሄድ ይች ወሬ ለጥ​ቅም አት​ሆ​ን​ህ​ምና” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ ኢዮአብን፦ የሆነ ሆኖ ኵሲን ተከትዬ፥ እባክህ፥ ልሩጥ አለው። ኢዮአብም፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም ወሬ የምትወስድ አይደለህምና ትሮጥ ዘንድ ለምን ትወድዳለህ? አለ።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:22
6 交叉引用  

ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፥ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው። ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ።


አሒማዓጽም፥ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፥ “ሩጥ!” አለው። ከዚያም አሒማዓጽ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ።


ንጉሡም፥ “ወጣቱ አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አሒማዓጽም፥ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም አገልጋይህን ሊልክ ሲል፥ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።


ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ጎድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤


እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ እግዚአብሔር ተገቢ ያልሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤


የሚያጸይፍ ነገር፥ ተራና የእንዝህላል ንግግርም ፈጽመው በመካከላችሁ አይኑሩ፤ ይልቁን አመስጋኞች ሁኑ።


跟着我们:

广告


广告