Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ሳሙኤል 18:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አንድ ሰው ይህን አይቶ ለኢዮአብ፥ “እነሆ፤ አቤሴሎም በባሉጥ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንድ ሰው ይህን አይቶ ለኢዮአብ፣ “እነሆ፤ አቤሴሎም በባሉጥ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዳዊት ወታደሮችም አንዱ ይህን አይቶ ለኢዮአብ “ጌታዬ፤ አቤሴሎምን በወርካ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁት!” ብሎ ነገረው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አንድ ሰውም አይቶ፥ “እነሆ፥ አቤ​ሴ​ሎም በዛፍ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥሎ አየሁ” ብሎ ለኢ​ዮ​አብ ነገ​ረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አንድ ሰውም አይቶ፦ እነሆ፥ አቤሴሎም በትልቅ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አየሁ ብሎ ለኢዮአብ ነገረው።

参见章节 复制




2 ሳሙኤል 18:10
6 交叉引用  

አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የባሉጥ ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፥ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ።


ኢዮአብም ይህን የነገረውን ሰው፥ “ምን አልህ! ካየኸው ታዲያ ለምንድን ነው ያኔውኑ መተህ ምድር ላይ ያልጣልኸው? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ፥ ዐሥር ብርና ዝናር እሸልምህ ነበር” አለው።


በዚህ ጊዜ አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ጋር ድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎም በበቅሎ ተቀምጦ ይሄድ ስለ ነበር፥ በቅሎዋ ጥቅጥቅ ያለ ቅርንጫፍ ባለው ትልቅ ባሉጥ ሥር በምታልፍበት ጊዜ፥ የአቤሴሎም ራስ በባሉጡ ቅርንጫፍ ተያዘ፤ የተቀመጠበትም በቅሎ በሥሩ ስታልፍ፥ እርሱ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠልጥሎ ቀረ።


ከእርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከጌታ በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በጌታ ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፥ “እሺ! እሰጣችኋለሁ” አለ።


መዓትስ ለኃጢአተኛ፥ መገለልስ ለሚበድሉ ሰዎች አይደለችምን?


ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ፥ ከሕግ እርግማን ዋጅቶናል፤ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው፤” ተብሎ ተጽፎአልና


跟着我们:

广告


广告