2 ሳሙኤል 11:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ከዚያም ዳዊት ኦርዮን፥ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ እደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮ በዚያ ዕለትና በማግስቱ በኢየሩሳሌም ቆየ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ከዚያም ዳዊት፣ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ ዕደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮን በዚያ ዕለትና በማግስቱም እዚያው ኢየሩሳሌም ቈየ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ዳዊትም “በል እንግዲህ የዛሬን እዚህ ዋል፤ ነገ ግን መልሼ እልክሃለሁ” አለው፤ ስለዚህ ኦርዮ በዚያን ቀንና በሚቀጥለው ቀን በኢየሩሳሌም ቈየ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ዳዊትም ኦርዮን፥ “ዛሬ ደግሞ በዚህ ተቀመጥ፤ ነገም አሰናብትሃለሁ” አለው። ኦርዮም በዚያ ቀንና በነጋው በኢየሩሳሌም ተቀመጠ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ዳዊትም ኦርዮን፦ ዛሬ ደግሞ በዚህ ተቀመጥ፥ ነገም አሰናብትሃለሁ አለው። ኦርዮም በዚያ ቀንና በነጋው በኢየሩሳሌም ተቀመጠ። 参见章节 |