Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ጴጥሮስ 2:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነዚህ ሰዎች ውሃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም ይጠብቃቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነዚህ ሰዎች የደረቁ ምንጮችና በዐውሎ ነፋስ የሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ የሚጠብቃቸውም ድቅድቅ ጨለማ ነው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እነዚህ ሰዎች ውሃ እንደሌለባቸው ምንጮች ናቸው፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚወሰዱ ደመናዎች ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማም ይጠብቃቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውሃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።

参见章节 复制




2 ጴጥሮስ 2:17
11 交叉引用  

ታላላቆቻቸውም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ላኩ፤ ወደ ጉድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፤ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ።


ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ! ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድርግልህ?


በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ።


የማይረባውን ባርያ በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት፤ በዚያ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።’


የመንግሥቱ ልጆች ግን ውጪ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


ከእንግዲህ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፥ በሰዎችም ማታለል ምክንያት፥ በነፈሰው የትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን፥ ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን፥ ሕፃናት መሆን አይገባንም።


ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፥ ወደ ጭጋጉና ወደ ጨለማው፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱ ገና አልደረሳችሁም፤


እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥


የመጀመሪያ ቦታቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘለዓለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ከጨለማ በታች ጠብቆአቸዋል።


跟着我们:

广告


广告