27 ስለዚህ ወደ ልጇ ጐንበስ አለችና በንጉሡ እያላገጠች በአባቶዋ ቋንቋ እንዲህ ስትል ተናገረች፤ “ልጄ ሆይ ዘጠኝ ወር በማሕፀኔ ለተሸከምሁህ ራራልኝ፤ ሦስት ዓመት አጠባሁህ፤ አሁን እስካለህበት ዕድሜ ድረስ እየመገብሁ አሳደግሁህ፤ ምንም ሳይጐድልህ ለዚህ አደረስኩህ።