20 እጅግ የምታስደንቅና ትውስታዋ የማይጠፋው እናትየዋ ናት፤ እርሷ ሰባቱም ልጆችዋ በአንድ ቀን ሲሞቱ እያየች ጸጥ ብላ ታገሰች፤ ምክንያቱም ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ ጥላ ስለ ነበር ነው።