23 እርሱ ግን ለዕድሜው የተስማማ የክብር ሥራ ለመሥራት ፈልጐ ከልጅነቱ ጀምሮ ሳያወላውል የኖረ፤ ይልቁንም በተቀደሰው የእግዚአብሔር ሕግ የጸና፤ በተከበረ ሸምግልናውና ሽበቱ ሥልጣን ያለው መሆኑን አውቆ ሳትዘገዩ ግደሉኝ ሲል መልስ ሰጠ፤