21 በበዓሉ ላይ የነበሩ ሰዎች ከብዙ ጊዜ ጀምሮ አልዓዛርን ያውቁት ስለ ነበር ገለል አደረጉትና ለመኑት፤ እርሱ መብላት የሚችለውን ሥጋ ከገዛ ቤቱ እንዲያስመጣና በንጉሡ እንደ በላ የታዘዘውን ሥጋ አሥመስሎ እንዲበላ መከሩት፤