Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ይዞት የሄደውም መልእክት “ይህ ደብዳቤ የእኔ ሠራዊት አዛዥ ስለ ሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከቆዳ በሽታ በማንጻት እንድትፈውሰው እፈልጋለሁ” የሚል ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ለእስራኤልም ንጉሥ የያዘው ደብዳቤ፣ “ከቈዳ በሽታ እንድትፈውሰው ይህን ደብዳቤ አስይዤ አገልጋዬን ንዕማንን ወደ አንተ ልኬዋለሁ” የሚል ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይዞት የሄደውም መልእክት “ይህ ደብዳቤ የእኔ ሠራዊት አዛዥ ስለ ሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከቈዳ በሽታ በማንጻት እንድትፈውሰው እፈልጋለሁ” የሚል ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፦ ደብ​ዳ​ቤ​ውን አደ​ረሰ። ደብ​ዳ​ቤ​ውም እን​ዲህ ይላል፥ “ደብ​ዳ​ቤው ካንተ ዘንድ በደ​ረሰ ጊዜ ባለ​ሟ​ሌን ንዕ​ማ​ንን ወደ አንተ ልኬ​ዋ​ለ​ሁና ከለ​ምጹ ፈው​ሰው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለእስራኤልም ንጉሥ “ይህች ደብዳቤ ወደ አንተ ስትደርስ ባሪያዬን ንዕማንን ከለምጹ ትፈውሰው ዘንድ እንደ ሰደድሁልህ እወቅ፤” የሚል ደብዳቤ ወሰደ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 5:6
3 交叉引用  

“እናንተ ለንጉሡ ተወላጆች ኃላፊዎች ናችሁ፤ ፈረሶችና ሠረገሎች የጦር መሣሪያዎችና የተመሸጉ ከተሞች ሁሉ በእናንተ እጅ ይገኛሉ፤ እንግዲህ ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ፥


ንጉሡም “ይህን ደብዳቤ ይዘህ ወደ እስራኤል ንጉሥ ሂድ” ብሎ ፈቀደለት። ስለዚህም ንዕማን ሠላሳ ሺህ ጥሬ ብር፥ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ምርጥ የሆነ ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፥ ጉዞውን ቀጠለ፤


የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቆዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።


跟着我们:

广告


广告