Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 5:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ወደ ቤት ተመልሶ ገባ፤ ኤልሳዕም “እስከ አሁን የት ነበርክ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “ጌታዬ፥ ኧረ እኔ የትም አልሄድኩም” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ከዚያም ገብቶ በጌታው በኤልሳዕ ፊት ቆመ። ኤልሳዕም፣ “ግያዝ ሆይ፤ የት ነበርህ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም፣ “አገልጋይህ የትም አልሄደም” ብሎ መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ወደ ቤት ተመልሶ ገባ፤ ኤልሳዕም “እስከ አሁን የት ነበርክ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “ጌታዬ፥ ኧረ እኔ የትም አልሄድኩም” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከዚ​ህም በኋላ ገብቶ፥ በጌ​ታው ፊት ቆመ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ግያዝ ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ወዴ​ትም አል​ሄ​ድ​ሁም” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እርሱ ግን ገብቶ በጌታው ፊት ቆመ፤ ኤልሳዕም “ግያዝ ሆይ! ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም “እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሄድሁም፤” አለ።

参见章节 复制




2 ነገሥት 5:25
14 交叉引用  

እርሱም፦ “የሦራ ባርያ አጋር ሆይ፥ ከወዴት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” አላት። እርሷም፦ “እኔ ከእመቤቴ ከሦራ የኮበለልሁ ነኝ” አለች።


ጌታም ቃየንን፥ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። እርሱም፥ “አላውቅም፥ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ?” አለ።


በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ፥ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።


ግያዝም “መምጣትስ በደኅና ነው የመጣሁት፤ ነገር ግን ጌታዬ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖሩ ሁለት የነቢያት ጉባኤ አባላት ድንገት በእንግድነት ስለ መጡበት፥ ሦስት ሺህ ብርና ሁለት መቀየሪያ ልብስ እንድትሰጣቸው እነግርህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል” ሲል መለሰለት።


ዖዝያንም ተቈጣ፤ የሚያጥንበትም ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በጌታ ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግምባሩ ላይ ለምጽ ታየ።


የአመንዝራ ሴት መንገድም እንዲሁ ነው። በልታ አፍዋን የምታብስ፦ “አንዳች ክፉ ነገርም አላደረግሁም” የምትል።


ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።


ሲበሉም ሳሉ “እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።


እራትም ሲበሉ፥ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው አሳብ ካስገባ በኋላ፥


በዚህ ጊዜ የሳኦል አጎት እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤ እንደማይገኙ በተረዳን ጊዜ ግን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው።


跟着我们:

广告


广告