Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




2 ነገሥት 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አካዝ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለማስደሰት ሲል ንጉሣዊ ዙፋን የሚዘረጋበትን ሉዓላዊ ስፍራ አስወገደ፤ ከዚያ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ወደ ቤተ መቅደስ ይገባበት የነበረውንም ልዩ በር ዘጋ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የአሦርንም ንጉሥ ለማስደሰት ሲል፣ በዕለተ ሰንበት ንጉሣዊ ዙፋን እንዲዘረጋበት በቤተ መቅደሱ ውስጥ የተሠራውን ከፍ ያለ ስፍራና ነገሥታቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚገቡበትን በውጭ ያለውን መግቢያ አነሣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አካዝ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለማስደሰት ሲል ንጉሣዊ ዙፋን የሚዘረጋበትን ሉዓላዊ ስፍራ አስወገደ፤ ከዚያ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ወደ ቤተ መቅደስ ይገባበት የነበረውንም ልዩ በር ዘጋ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የዙ​ፋ​ኑን መሠ​ረት ሠራ፤ ስለ አሦ​ርም ንጉሥ በውጭ ያለ​ውን የን​ጉ​ሡን መግ​ቢያ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አዞ​ረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በእግዚአብሔርም ቤት የዙፋኑን መሠረት ሠራ፤ ስለ አሦርም ንጉሥ በውጭ ያለውን የንጉሡን መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት አዞረው።

参见章节 复制




2 ነገሥት 16:18
7 交叉引用  

በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዓይነት፥ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፥ የቤተ መንግሥቱን ሠራተኞች የሥራ አደረጃጀት፥ የደንብ ልብሳቸውንም ዓይነት፥ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም የሚያቀርባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀችው በላይ ነበር።


የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጣቸው፤ “በሰንበት ቀን ለዘብ ጥበቃ በምትሰማሩበት ጊዜ ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤


ንጉሥ አካዝ በቤተ መቅደስ ውስጥ መገልገያ የነበሩትን ከነሐስ የተሠሩ መንኰራኲሮች ቆርጦ ልሙጥ የሆነውን ነገር ከጐናቸው ወሰደ። በእነርሱ ላይ የነበሩትንም የመታጠቢያ ሳሕኖች ወሰደ፤ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ከታች በኩል ተሸክመውት ከነበሩት ከነሐስ ከተሠሩት ከዐሥራ ሁለት የበሬ ቅርጾች ጀርባ ላይ አንሥቶ፥ ከድንጋይ በተሠራ መሠረት ላይ አኖረው።


ንጉሥ አካዝ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤


እስከ ዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ሰፍረዋል፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በርም ጠባቂዎች ነበሩ።


መስፍኑ ብቻ በጌታ ፊት ምግብ ለመብላት ይቀመጥበታል፤ በበሩ መተላለፊያ መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል።


መስፍኑ ከውጭ በኩል ባለው በር በመተላለፊያ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፥ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ፤ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።


跟着我们:

广告


广告